call us now

251 911 23 08 57 / 60 76 06

The child and the caregiver

የቀዳማይ ልጅነት እደገትና የመምህሩ ሚና፡-

አንዱ የመምህር ተግባር የቀዳማይ ልጅነት እደገት ሂደትን ተረድቶ ማጎልበት ነው፡፡ ይህ ሂደት የሕጻናት አዕምሮ የሚለጠጥበትና የሚለወጥበት፤ ሕጻናት ከአካባቢያቸው ጋር በሚያደርጉት መስተጋብርና በሚያገኟቸው ማነቃቂያዎች የአዕምሮ ሴሎቻቸው እርስ በርስ የሚገናኙበት፣ የሚናበቡበት፣ የመማር ፍላጎታቸው መሠረት የሚጣልበት፣ የሕይወት ክሂሎት፤ ጥበብ፣ ችሎታና ማህበራዊ ግንኙነት መስፋት የሚጀምርበት ወቅት ነው፡፡ ይህን ተርድቶ የሕጻናትን አዕምሮ ለማበልፀግ መጣር የመምህር ተግባር ነው፡፡ ወደ ግብ ለማምራት ስራን በትኩረት በማከናወን (Focusing)፣ ጤናማ የባህርይ ለውጥ የሚያስከትል የእውቀት ሽግግር በማከናወን (Mediation of Meaning)፣ እውቀትን በማሻሻልና በማስፋፋት (Transcendence)፣ የሕፃናት የብቃት ስሜት እንዲዳብር በማስቻል (Mediation of Competence)፣ ባሕርያትን በመከታተል፣ በመቆጣጠርና ልምድን በማዳበር (Regulation of Behavior) የሕፃናትን ሰብዕና መቅረጽ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም መሠረታዊ የእውቀት ማሸጋገሪያ ዘዴዎች (መዝሙሮች፤ ዘፈኖች፤ የሚያዝናኑ ቀልዶች፤ የተለያዩ ጨዋታዎች፤ ሥዕሎች፤ ትምህርታዊ ንግግሮች፤ የፈጠራ ሥራዋች፤ ትርጉሞችና ማብራሪያዎች፤ ጥያቄና መልሶች፤ ዘገባዎች፤ የሰውነት እንቅስቃሴዎች፤ ማበረታቻዎች፤ ጭፈራና ዳንሶች፤ አዳዲስ ግኝቶች፤ የእንግዳ ግብዣዎች፤ ተደጋጋሚ ሙከራዎችና ልምዶች፤ ትዕግስትና ምክንያታዊነት……ወዘተ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ውስጥ የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ እያንዳንዱ የእድገት ስኬት ሕጻኑን ለቀጣይ የእድገት ሂደት ያዘጋጀዋል፡፡ ምንም እንኳ በሕጻናት መካከል ግላዊ የሆኑ ልዩነቶች ቢኖሩም አጠቃላዩ የእድገት ሂደት ጉዞ ግን ለሁሉም ተመሳሳይ ነው፡፡ የሕጻናት ጤናማ እድገት ወደ ላይ የማደግ አቅጣጫን ያመለክታል፡፡ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ለሕጻናት ጤናማ እድገት አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ስነልቦናዊና ፔዳጎጅካዊ አቀራረቦችን መተግበር ጠቃሚ ነው፡፡

መልካም፣ መልካሙን ለሕታናት!

ሳህሉ ባዬ

www.enrichmentcenters.org

 


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”