call us now

251 911 23 08 57 / 60 76 06

ሕፃናት የመጡበት ቤተሰብ ሁኔታ

ሕፃናት የመጡበት ቤተሰብ የቅርብ ግንኙነት የተጠናከረበትና ፍቅር የሰፈነበት ከሆነ አዲሱን አካባቢ ተቀብሎ ከሌሎች ለመቀላቀልና ለመዋሐድ የተሻለ ዝግጁነት ሊኖራቸውና ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ በቤታቸው ውስጥ ያሳለፉት ምቹ የሕይወት ቆይታና ያገኙት ልምድ ዓለም አመቺ የመኖሪያ ቦታ መሆኗን፤ ሌሎችንም ማመን የማይጎዳና ጠቃሚ መሆኑን እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ዘወትር ገደብ የለሽ ቅጣትን፣ መከፋትንና ቅሬታን ማስተናገድ ባህሉ ከሆነ ቤተሰብ ውሰጥ የመጡ ሕጻናት መጀመሪያ መምህራንና አዲሱን አካባቢ ሊጠራጠሩ ይችላሉ፡፡ በዚህ ወቅት ለእነዚህ አይነት ሕጻናት ከፍተኛ ትዕግስት ሊኖረንና የምንችለውን ያህል የጋለ ፍቅርና መረጋጋት ልንለግሳቸው ይገባል፡፡ ሦስት እጅ የሆነውን የት/ቤት ውስጥ ደህንነትንና የእንክብካቤ ተግባራትን በበርካታ መንገዶች ማስፈን ይቻላል፡፡

መልካም፣ መልካሙን ለሕፃናት!!!

መምህር ሣህሉ ባዬ

   www.enrichmentcenters.org


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”