ይደረስ ለአፀደ ሕፃናት መምህራንና ረዳት መምህራን
የአጸደ ሕጻናት መምህራንና ረዳት መምህራን መሆናችን፣ ለመሆን ማሰባችንና ሕጻናትን መውደዳችን ሕፃናት ከእኛ ጋር በሚሆኑ ወቅት ተደስተውና አዕምሯዊ መነቃቃት አግኝተው በት/ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ይረዳል፡፡ የሕጻናትን ባሕርያት ይበልጥ እየተረዳን በሄድን ቁጥር እነርሱን ለመምራት ወይም አቅጣጫ ለማስያዝ ብቁ እንሆናለን፡፡ ስለ እያንዳንዱ ሕፃን ቤተሰባዊ መሠረት፣ ያለፈ ታሪክና ልምድ የምንችለውን ያህል ለማወቅ ጥረት በማድረግ የሕጻኑን ሁኔታ ይበልጥ ለመረዳት እንጣር፡፡ ጠቃሚው ነገር በእኛ እንክብካቤ ሥር የሚገኙ ሕጻናት ከእኛ ጋር ሲሆኑ ደህንነትና ምቾት የሚሰማቸው መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ከአሳዳጊዎቻቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው ሲነጠሉ ለአብዛኞቹ ሕፃናት የመጀመሪያ ተሞክሯቸው ነው፡፡ አንዳንድ ሕጻናት በአዲሱ ሁኔታና አካባቢ እርግጠኛ ስለማይሆኑ ይፈራሉ፡፡ በአፀደ ሕፃናት ቆይታቸው ከሚያገኟቸውና ከሚነካኳቸው ነገሮች ይልቅ በቅድሚያ ከለላና እንክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡
መልካም፣ መልካሙን ለሕፃናት!!
ሣህሉ ባዬ ዓለሙ
Comments