call us now

251 911 23 08 57 / 60 76 06

Child - teacher interaction

ወላጆች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ የመስጠት አስፈላጊነት፡-

ከወላጆች ለሚነሱ ጥያቄዎች አስፈላጊውን መልስ በወቅቱ ማስረዳት አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ ወላጆች ከአጸደ ሕጻናት ውጪ እንዲሆኑ አናስገድዳቸው፡፡ የልጆችን የት/ቤት ውሎ ለወላጆች መግለጽ የመምህራን ተግባር ነው፡፡ ከሁሉም በላይ የምናስተምራቸው ሕጻናት የእነርሱ ልጆች ስለሆኑ በሕይወታቸው ከልጆቻቸው በላይ የሚወዱት ነገር አለመኖሩን መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው ት/ቤቶች እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ መብት አላቸው፡፡ ት/ቤቱን እንዲጎበኙና ፈቃደኛ ከሆኑም ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማበረታታት ወላጆችን በ “እንኳን ደህና መጡ” አቀባበል ምቾት መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የዋላጆችን ስሜት መቀየር የልጆቻቸውን ስሜት ይቀይራል፡፡ ልጆች ከወላጆች በላይ የሚወዱት የለምና ወላጆቻቸው የሚደሰቱ መሆናቸውን ካስተዋሉ ሁሌዬ በት/ቤት ውስጥ ለመገኘት ፈቃደኞች ይሆናሉ፡፡ በአጠቃላይ ከመምህራንና  ወላጆች ጤናማ ግንኙነት ተጠቃሚ ሕጻናት ናቸው፡፡ ወላጅ መሆን ቀላል ነገር ስላልሆነ ለወላጆች ስሜት ተገቢ ክብርና ድጋፍ መስጠት፣ የግል ጉዳያቸውን ለማካፈል ፍላጎት ካሳዩ ደግሞ በአክብሮትና በጥሞና ማደመጥና ከተቻለ አረጋጊና አዝናኝ ሆኖ መቅረብ የሞያ ግዴታ ነው፡፡ መረጃ እንዳይባክን ግን በሚስጥር መጠበቅ አለበት፡፡ የሞያ አጋር ካልሆነ ሰው ጋር መወያየት አይመከርም፡፡

መልካም፣ መልካሙን ለሕታናት!

ሳህሉ ባዬ

www.enrichmentcenters.org


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”