Parents participation
የወላጆች ተሳትፎ አስፈላጊነት፡-
ሕጻናት በት/ቤት ቆይታ የተማሩትንና ያከናወኑትን ወላጆች እንዲመለከቱና ከተቻለም እንዲተገብሩ ማድረግ ይጠቅማል፡፡ እነዚህ መድረኮች ወላጆች የልጆቻቸውን ሙከራና ጥረት ማወቅ ያስችሏቸዋል፡፡ ዘወትር ለሕጻናት የሚደረግ የሞቀ አቀባበልና አሸኛኘት ለሥራ የሚደረግን ጥንቃቄና የሚሰጥን ትኩረት ይገልጣል፡፡ ወላጆች ለአፀደ ሕጻናት ጠቃሚ ሀብት ናቸው፡፡
አንዳንድ ወላጆች በክፍል ውስጥ ለሕፃናት ታሪክ በመተረክ፣ ተረት በማውጋት፣ ዘፈኖች በመዝፈን፤ ዜማዎች በማዜም ወይም በመዘመር ነፃ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ወላጆች የሙዚቃ መሳሪያዎች በመጫወትና ያልተለመዱ ብርቅዬ ተወዳጅ እንስሳትን በማስተዋወቅ፣ አንዳንድ ወላጆች ምግብ በማዘጋጀትና በማብሰል፣ አንዳንድ ወላጆች የስብሰባ እቅድ በማዘጋጀት፣ ግልፅና ወዳጃዊ የሆኑ ወላጆች ደግሞ ልምዳቸውን በማካፈል የትምህርት መርሐ-ግብር ያጎለብታሉ፡፡ ለወላጆች የተዘጋጀው ፕሮግራም ምንም ይሁን ምን ለባህል፣ ለዘር፣ ለጎሳ፣ ለብሔር፤ ለብሔረሰብና ለኃይማኖታዊ ልዩነቶች አክብሮት መስጠት በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡ የወላጆች ምርጫ ምንም ይሁን ምን ምርጫቸውን ማክበር ተገቢ ነው፡፡ ይህን እድል ስንጠቀም ባለን እውቀት ላይ ተጨማሪ እውቀት አገኘን ማለት ነው፡፡
መልካም፣ መልካሙን ለሕታናት!
ሳህሉ ባዬ
Comments