call us now

251 911 23 08 57 / 60 76 06

ሕጻናት ለወላጆቻቸው የደስታና ስኬት ምንጭ፣ ለሀገራቸው ቃልኪዳን ናቸው።

ሕጻናት ለወላጆቻቸው የደስታ፣ ፍስሃና ስኬት ምንጭ ሲሆኑ ለሀገራቸው ደግሞ ተስፋና ቃል-ኪዳን ናቸው፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ምኞትና ተስፋ የሰነቁ በመሆናቸው በአጸደ ሕፃናት ቆይታቸው የመምህራንን ጥበቃና እንክብካቤ እያገኙ እንዲማሩላቸው የሚሳሱላቸውን ልጆች ለት/ቤቱና ለመምህራን በአደራ ያስረክባሉ፡፡ እንደ ወላጆቻቸው ሕጻናትም የራሳቸውን ተስፋና ምኞት የሰነቁ ስለሆነ ካልተገደቡ በቀር መማር፣ ማወቅና ውጤታማ መሆን ይሻሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሕጻናት ወደፊት ስለሚሆኑት ጉዳይ ማንኛውም ሰው በእርግጠኝነት ሊናገር/ ዋስትና ሊሰጥ/ ቃል ሊገባ አይችልም፡፡ ሆኖም ለጊዜውም ቢሆን እነኝህ ሕጻናት በእኛ ቁጥጥርና ክብካቤ ሥር ስለሆኑ በምቹ ሁኔታ ላይ በተገነባ የሞቀ ወዳጃዊ ስሜት አስፈላጊውን እውቀት ሰጥተንና ኮትኩተን ማሳደግ የእኛ የመምህራን የሥራ ድርሻ ስለሆነ አንዳንዴ የቡድን አስተምህሮት ዘዴን፤ አንዳንዴ ደግሞ የአንድ ለአንድ ያስተምህሮት ዘዴን እንጠቀም፡፡ ይህን ከመተግበራችን በፊት ግን ከምንም በላይ ስለ ሕፃናት ጠንቅቀን ማወቅ የሚገቡንን እውነታዎች ተረድቶ ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡

መልካም፣ መልካሙን ለሕፃናት!!

ሣህሉ ባዬ ዓለሙ

www.enrichmentcenters.org


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”