ስለ ሕጻናት አንዳንድ እውነታዎች
ታዋቂዋ የቶለራንስ ካሊፎርኒያ ሄራልድ ጋዜጣ አምደኛ ዶርቲ ሎውናታል እ.ኤ.አ በ1954 ዓ.ም “Creative Family Living” በሚል ርዕስ ስር ያሰፈረቻቸውን ምክሮች ማጤኑ በጣም ጠቃሚ ነው።
አንድ ሕጻን
- ከወቀሳና ትችት ጋር ካደገ፣ ማውገዝንና መንቀፍን ይማራል፤
- በፍርሃትና ስጋት ካደገ፤ ጭንቀትን ይማራል፤
- ከጥላቻ ጋር ካደገ፣ ጠብን ይማራል፤
- ከሐዘንና ፀፀት ጋር ካደገ፣ በራሱ ላይ እያዘነ መኖርን ይማራል፤
- እየተፌዘበት ካደገ፤ ዓይን አፋርነትን፣ ድንጉጥነትንና ደንጋራነትን ይማራል፤
- ከቅናት ጋር ካደገ ምቀኝነትን ይማራል፤
- ከሀፍረትና ውርደት ጋር ካደገ ጥፋተኛነትንና ሀጢያተኛነትን ይማራል፤
- እየተበረታታ፣ እየተደፋፈረና እየተነቃቃ ካደገ በራስ መተማመንን ይማራል፤
- ከትዕግስትና መቻቻል ጋር ካደገ ቻይነትንና ጥንቁቅነትን ይማራል፤
- ከምስጋና ጋር ካደገ ማድነቅን ይማራል፤
- ከተደማጭነት ጋር ካደገ አፍቃሪነትን ይማራል፤
- ከመፍቀድና ማፅደቅ ጋር ካደገ እራስን መውደድና መቀበልን ይማራል፤
- እውቅና እያገኘ ካደገ የዓላማ ጠቃሚነትን ይማራል፤
- ያለውን ከማካፈልና ከመረዳዳት ጋር ካደገ ደግነትን፣ ቸርነትን ወይም ለጋስነትን ይማራል፤
- ከቅንነት፣ ታማኝነትና ሚዛናዊነት ጋር ካደገ እውነተኛነትና ፍትሃዊነትን ይማራል፤
- በመልካም አያያዝና ደኅንነት ካደገ በራሱና እርሱን በተመለከቱ ጉዳዮች እምነት ይኖረዋል፤
- አንድ ሕጻን ከወዳጃዊ አቀራረብና ጨዋታ ጋር ካደገ ዓለም ምቹ የመኖሪያ ስፍራ መሆኗን ይማራል፤
- እርስዎ ከመንፈስ እርካታ ጋር የሚኖሩ ከሆነ፣ ልጅዎ በሰላማዊ አእምሮ ውስጥ ይኖራል፡፡ “Creative Family Living”, Source: Is it tomorrow yet? by Elinor Ami Columbus
መልካም፣ መልካሙን ለሕፃናት!!
ሣህሉ ባዬ ዓለሙ
Comments