እያንዳንዱ ሕጻን ከሌላው ይለያል
እያንዳንዱ ሕጻን ከሌላው የሚለይበት ልዩ ሰብዕና አለው። ባህርይውን የሚያንፀባርቅበት የራሱ መንገድ አለው፡፡ ለምሣሌ ከሌሎች ሕጻናት ጋር እንዴት እንደሚቀላቀል ወይም እንደሚተባበር ልብ እንከታተል፡፡ በአቋሙ የሚጸና ግትር ነው? ወይስ ይደራደራል? ለመስማማት ይጥራል? የሌሎችን አስተያየት ይቀበላል? ያከብራል? ይስማማል? ወይስ የራሱን ሐሳብ ብቻ በሌሎች ላይ ለመጫን ሁልጊዜ ይወተውታል? ወይስ በራሱ መንገድ ብቻ መሄድን ይመርጣል? ወይስ ለሌላ ሀሳብ በቀላሉ እጁን በመስጠት ለመብቱ አይቆምም? ሕጻናትን ይበልጥ በቀረብናቸውና ባወቅናቸው መጠን ስለ ሁኔታቸው የመረዳት ዕድል እናገኛለን። እያንዳንዱ ሕጻን በየትኛው የእድገት ሂደት ላይ እንደሚገኝ ለመገንዘብ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርናል፡፡ ለወላጆችም እንደዚሁ።
መልካም፣ መልካሙን ለሕፃናት!!
ሣህሉ ባዬ ዓለሙ
Comments