call us now

251 1 911 23 08 57 / 60 76 06

Children and Black Box (Part 1)

መልዕክተ - ትምህርት 16

የሕፃናት ይወትና ጥቁር ሳጥን (Black Box):-

በሣህሉ ባዬ

(ክፍል 2)

 

   በመልዕክተ-ትምህርት 15 ክፍል አንድ መልዕክታችን የጨቅላ ሕፃንነት ጤናማ እድገትን የሚያቀጭጩና “በጥቁር ሳጥን (Black Box)” ውስጥ እንዳሉ ስለሚነገርላቸው መርዛማ የጤናማ እድገት ጠንቆችና ስለአሉታዊ ተፅዕኗቸው መዳሰሳችን ይታወሳል። በዛሬ መልዕክደግሞ መርዛማ ሁኔታዎችና ጓጂ ተፅዕኗቸው መካከል ስላለው ጠንካራ ትስስር ጥናቶችን በማጣቀስ ለማየት እንሞክራለን

   በመጀመሪያ የምንመለከተ የጥናት ሰነድ በተበደሉ፣ ተንገላቱ ተጓሳቆሉ፣ ተረሱና ለተለያዩ ተደራራቢ መርዛማ ማበራዊ ችግሮች በተጋለጡ፣ ሕይወታቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ ምክንያት የማህበረሰብ-አቀፍ ድጋፍና እንክብካቤ በሚደረግላቸውና እድሜያቸው ሦስት ዓ በሞላቸው አሜሪካዊ ሕፃናት ላይ የተካሄደ ጥናትን ይሆናል። የጥናቱ ዓላማም ድርብርብ መርዛማ ችግሮች በጨቅላ ሕፃናት ላይ ሲከሰቱ የሚያስከትሉትን ዘላቂ የጤና ጠባሳ መፈተሽ ነበር። በተደረገው ሳይነሳዊ ፍተሻም ጨቅላ ሕፃናት 6 ወይም 7 አስቸጋሪ የህይዎት ፈተናዎች ሲጋለጡ ከ90 እስከ 100 ፕርሰንት በሚደርስ መጠን በስሜ፣ በማህበራዊ፣ በግንዛቤ፣ በዕውቀትና በቋንቋ ድገታቸው በእጅጉ የተጓዱ እንደሚሆኑ ተረጋግጧል

      በሁለተኛው ጥናት የተካሄደው “ዱንዲ” በምትባል ትንሽ የኒዩዚላንድ ከተማ ውስጥ ነበር። ይህ ጥናት በዱንዲ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሰ - ጡር (እርጉዝ) እናቶችን ከፅንስ ጀምሮ የነበራቸውን የጤና ክትትል ታሪ የልጆቻቸውን የ32 ዓመት የጤና መረጃዎች ያካተተ ነበር። የጥናቱ ዓላማም በፕላዝማ (በደም ውሃ) ውስጥ የሚገኜውን “ሲ - ሪአክቲቭ ፕሮቲን (C-Reactive Protein)” በመባል የሚታወቀውን ንጥረ ነገር ማጥናት ነበር። ንጥረ ነገ የሰውነትን የመመረዝ ወይም የመጉረብረብ ደረጃ ጠቋሚ ነው (እንደ ችግሩ ሁኔታ የንጥረ ነገሩ ምጠን ክፍና ዝቅ ሊል ይችላል)፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው ለተደራራቢ መርዛማ የሕይወት ፈተናዎቸ ተጋላጭ የነበሩ ጨቅላ ሕፃናት በእድሜ ከፍ ሲሉ ለልብ ሕመም የሚጋለጡ መሆናቸውን አሳይቷል በዚሁ ጥናት የ32 ዓመታት የጤና ታሪካቸውና የ”ሲ-ሪአክቲቭ ፕሮቲን” መጠናቸው ከተፈተሸላቸው ጤናማ ጓልማሶች መካከል 15% በሚሆኑሰዎች ደም ውስጥ ከፍተኛ “ሲ - ሪአክቲቭ ፕሮቲን” ተገኝቷል። ይህ ክስተት ከዘር ውርስ የመጣና ሰዎቹም ለልብ ድካም ሕመም የተጋለጡ መሆናቸው ታውቋል ከዚህ በተጨማሪ እድሜያቸው 32 ዓመት የሞላቸውና የክሊኒካል ጭንቀትና የአእምሮ መደንዘዝ ምርመራ ተደረገላቸው መካከል 30% በሆኑት ላይ ከፍተኛ “ሲ-ሪአክቲቭ ፕሮቲን” የተገኜባቸው ሲሆን በባህሪያቸውም በክሊኒካል ጭንቀት፣ ተከታታይ የአእምሮ ድብርትና ቁጡነት የሚሰቃዩ ሰዎች ሆነው ተገኝተዋል። በሕፃናት ላይ የተደረግው ጥናትም እንዳረጋገጠው በጨቅላ ሕፃንነት ሕይወት በደል፣ እንግልትና ድብርት በደረሰባቸውና እድሜያችው 32 ዓምት በሆናቸው ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት 40% የሚሆኑት ሰዎች በጣም ከፍ ያለ “ሲ-ሪአክቲቭ ፕሮቲን” ተገኝቶባቸዋል።

    በአጠቃላይ ከፍ ብለን የጠቀስናቸው ጥናቶች የሚጠቁሙ ቁምነገር በሕፃነት እድገት ሂደት የሚያጋጥሙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እስከ እርጅና ዘመን የሚዘልአካላዊአእምሯዊ የጤና ጉዳቶችስከተል ይል ያላቸው መሆኑ ነው። አካል በጨቅላ ሕፃንነት ዘመየደረበትን ጠባሳዎች የማስታወስ ተፈጥሯዊ ችስላለው ቀደም ሲል የደረበትን አእምሯዊ፣ ማህበራዊ፣ ሥነልቦናዊ፣ ስሜታዊና አካላዊ ጉዳቶች ፈፅሞ አይራሳም የጠቀስናቸውን ጥናቶች አስፈላጊነት በተመለከተ ፕሮፌሰር ጃክ ሸንኮፍ የሚከተለውን ይላሉ። እነዚህ ጥናት ውጤቶች በአስቸጋሪና ቅስም ሰባሪ መርዛማ ነገሮች የታጨቀውን ጥቁር ሳጥን (Black Box)ከፍተን እንድንፈትሽና በሚያስከትሉትይወት ጠባሳ ላይ በቂ መረጃ ለማግኜት የሚረዱን መግቢያ በሮች ናቸው ይላሉ፡፡ ፕሮፌሰር ዣክ በመቀጠል ለምንድን ነው በሕፃንነታቸው ለመርዛማ ችግሮች የተጋለጡ ሕፃናት በጓልማሳነት ዕድሜያቸው ር በሰደዱ የጤና መታወኮች የሚሰቃዩት? ለምንድን ነው ለደም ግፊት የጤና ችግር የሚጋለጡት? ለምንድን ነው ለስኳር በሽታ ተጠቂ የሚሆኑት? ለምንድን ነው እረዥም እድሜ የማይኖሩት? ለምንድን ነው በይወት የመኖር የእድሜ ጣሪያቸው አነስተኛ የሆነው? የሚሉ ጠቃሚ ጥያቄዎችን በማንሣት ይሞግታሉ፡፡ ለነዚህና መሰል ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ ሙያዊ ትንታኔዎቻቸውን በሚቀጥለው መልዕክታችን ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን። እስከዚያው በአስቸጋሪ ሕይወት ውስጥ ያሉ ሕፃናትን የምናስብበት፣ ለአገራችን ሰላም እንዲሰፍን የምንፀልይበት ፍቅር ሰጥተን የምንቀበልበት የገና በዓል በመመኜት ተሰናበት!!

 

መልካም፣ መልካሙን ለሕፃናት!!

ሣህሉ ባዬ ዓለሙ

የፕሮጄክት ማኔጅመንት፣ የሕፃናት ዕድገትና ነልቦና ባለሙያ

www.enrichmentcenters.org

 

 

 


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”