call us now

251 1 911 23 08 57 / 60 76 06

መልዕክተ - ትምህርት 9

የኢትዮጵያዊ ሕፃናት ህይወት ሲዳሰስ

  የሁለተኛው ዓለም ጦርነት መገባደጃ አገራችን አትዮጵያ በአዲሱ ዓለም አቀፋዊ የለውጥ ስርዓት ውስጥ በመሳተፍ ኢኮኖሚዋን፣ የትምህርት ሥርዓቷን፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዋን….ወ.ዘ.ተ ማፋጠን የጀመረችበት ወቅት ነበር፡፡ ይህ ጊዜ የተፈጠረውን ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ተከትሎ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወደ ሃገር ገብተው የልማት አካል አንዲሆኑ የተጋበዙበት ጊዜ ነበር፡፡ ይህንኑ ዲፕሎማሲያዊ ግብዣ ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች (ዩ.ኒ.ሴ.ፍን ጨምሮ) በጤና፣ ትምህረትና ግብርና ፕሮግራሞች ላይ ለመሳተፍ የሚያስችሉ ጉብኝቶችን እ.ኤ.አ ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ ማድረጋቸውንና እ.ኤ.አ. በ1958 ዓ.ም ዩ.ኒ.ሴ.ፍ ጽ/ቤቱን በአዲስ አበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍቶ ይፋዊ ሥራ መጀመሩን እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም የታተመው ዓመታዊ የዩ.ኒ.ሴ.ፍ ሪፖርት አስነብቦናል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮም የሕፃናቶቻችን ጉዳይ ኦፊሴላዊ ትኩረት ማግኜት ጀመረ፡፡  

  ዩ.ኒ.ሴ.ፍ በሴፕቴምበር 2015 ዓ.ም “UPDATED NATIONAL EQUITY SITUATION ANALYSIS ON CHILDREN AND WOMEN IN ETHIOPIA” በሚል ርዕስ ባሳተመው ሰነድ ላይ እናዳመለከተው 90 ሚሊዮን ከሚሆነው የሃገራችን ህዝብ መካከል 48% ሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ ምንም እንኳን አገሪቱ በድህነት ቅናሳ ላይ አበረታች መሻሻልን ብታሳይም 26% የሚሆነው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር መሆኑን ተጠቁሟል፡፡ ዕለታዊ ገቢውም ከአንድ የአሜሪካ ዶላር ያነሰ 0.60 የአሜሪካ ሳንቲም ነበር፡፡ በገጠር ከሚኖረው ህዝብ መካከል 46% ያህሉና በከተማ ከሚኖረው ህዝብ መካከል 27% ያህሉ በከፋ የድህነት ህይወት ውስጥ እንደሚኖር ታውቋል፡፡ በሕፃናት ላይ የተመዘገበው የድህነት መጠንም ከሃገሪቱ ህዝብ የድህነት ደረጃ ጋር ሲነፃፀር 34.4% ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ ሕፃናቶቻችን እንደሚከተለው ለተዘረዘሩት ችግሮች የተጋለጡ ናቸው፡፡

  1. የተመጣጠነ ምግብ፣
  2. ንፁህ የመጠጥ ውሃ፣
  3. አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃጦች፣
  4. የጉልበት ብዝበዛ፣
  5. ሕገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውር፣
  6. የጤና አገልግሎት፣
  7. ጥራት ያለው የትምህርት አገልግሎት፣
  8. የህግ ከለላ፣
  9. መቀንጨር - በገጠር ከሚኖሩት 42%፣ በከተማ ከሚኖሩት 27% ያህሉ ሕፃት በመቀንጨር ችግር የሚሰቃዩ ሲሆን ከ5 ዓመት ዕድሜ በታች ከሚገኙ 10 ሕፃናት ውስጥ አራቱ ለመቀንጨር አደጋ የተጋለጡ መሆናቸው ታውቀዋል፡፡ እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች የልጆቻችንን ብሎም የሃገራችንን የወደፊት እጣ-ፋንታ ወሳኝ መሆናቸው ተረጋግጧል፡

     ቀደም ሲል እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም በታተመ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ፈንድ ዓመታዊ ሪፖርት መሠረት ከስሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት የሚኖሩ ሕፃናት ህይወት ከሌላው የዓለማችን ክፍል ከሚኖሩ ሕፃናት ህይወት ጋር ሲወዳደር ከስሃራ በታች ያሉ ሕፃናት ችግሮች በእጅጉ የከፉ ስለመሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም ለእነዚህ ችግሮች ሰለባ መሆኗ ተሰምሮበታል፡፡ የእነዚህ ችግሮች ተሸካሚ ከሆኑት አፍሪካዊ ሕፃናት መካከል 48.3% ያህሉ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች በሞት ያጡ፣ ከ200 ሚሊዮን የሚልቁ ሕፃናት ደግሞ ተሰጥዖዋቸውን ማበልፀግና መጠቀም ያልቻሉ፣ 60% ያህሉ ደግሞ ከአያቶቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ጋር የሚኖሩና የመንገድ ላይ ተዳደሪዎች መሆናቸውን VanJzendoorm የተባሉ ተመራማሪ እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም በሰነዱት የጥናት ሰነድ ላይ አስፍረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እ.ኤ.አ በ2010 ዓ.ም EuroChild በሚል ስያሜ የሚጠራ አለም አቀፍ ተቋም ባደረገው ጥናት በአፍሪካ ውስጥ የተፈጠሩ ዕድሚያቸው ከ3 ዓመት በታች የሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ለጋ ሕፃት ወደ ሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት (Orphanages) ይወረወራሉ ሲል የህይወታቸውን አስከፊነት ገልፆታል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም እነዚህ ችግሮች ጎልተው ከሚታዩባቸው ሃገራት ተርታ መገኜቷን ከሰነዱ ተረድተናል፡፡ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ Miller በመባል የሚታወቁ ተመራማሪ እ.ኤ.አ. በ2008 ዓ.ም ባከናወኑት ጥናት ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛትና ለችግር በተጋለጡ ሕፃናት ቁጥር ከአፍሪካ 2ኛ ነች ሲል ጠቁመዋል፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተውና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እነደዘገቡት ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና ተንከባካቢ የሌላቸው አትዮጵያዊ ሕፃናት ቁጥር በወቅቱ 5, 029, 000 (አምስት ሚሊዮን ሃያ ዘጠኝ ሽህ) እነደነበር ተጠቅሷል፡፡ ከነዚህ ሕፃናት መካከል ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ 200,000 ሽህ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ 150,000 ሽህ ያህሉ ደግሞ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ይኖሩ እነደነበር ተዘግቧል፡፡ ዛሬስ ??? መረጃዎችን አሰባስቤ ብቅ ለማለት እሞክራለሁ፡፡ ቸር ይግጠመን!

ሰላምና መልካሙን ሁሉ ለሕፃናትና ለሃገሬ ተመኘሁ!!

ሣህሉ ባዬ

www.enrichmentcenters.org

የፕሮጄክት ማኔጅመንት፣ የሕፃናት ዕድገትና ስነልቦና ባለሙያ

 

 


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”