call us now

251 1 911 23 08 57 / 60 76 06

መልዕክተ - ትምህርት 11

የኢትዮጵያዊ ሕፃናት ህይወት ሲዳሰስ (ክፍል 3)

       የዚህምን ችግር አስከፊነትና ቀጣይነት በተመለከተ “Nutritional Status of under Five in Ethiopia: A systematic Review and Meta-Analysis” በሚል ርዕስ Ahmed Abdulahi, Sakineh Shab-Bidar, and Kurosh Djafarian የተባሉ ተመራማሪዎች ዕድሚያቸው ከ0-5 ዓመት ዕድሜ ክልል የሚገኙ 39,385 ሕፃትን በናሙናነት ወስደው ባከናወኑትና በ“Ethiopian Journal of Health Sciences” በሚባል ጆርናል ላይ ለህትመት ባበቁትና የመቀንጨርን፣ የመመንመንንና የክብደት ማነስን ስርጨት በዳሰሱበት ጥናታቸው እነዳረጋገጡት በጥናቱ ከተካተቱት ሕፃናት መካከል 40% ያህሉ የመቀነጨር፣ 33% ያህሉ የክብደት ማነስና 19% ያህሉ ደግሞ የመመንመን ችግሮች ተሰተውሎባቸው ተገኝተዋል፡፡ ጥናቱ እንደተነተነውም የመቀንጨርና የክብደት ማነስ ችግሮች እ.ኤ.አ ከ2010 - 2014 ዓ.ም ባሉት ዓመታትም ይበልጥ ስር የሰደደ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ጥናት እነደተገለፀው ለክብደት ማነስና መቀንጨር ምክንያቶች ናቸው ተብለው የተዘረዘሩት የተጨማሪ ምግብ እጦት፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ ተቅማጥ፣ የእናቶች አለመማር፣ የመኖሪያ አካባቢ፣ ማህበረዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ናቸው፡፡ ከ2014ዓ.ም ወዲህም የምግብ እጥረት ችግር መሻሻል ያልታየበት፣ ከወትሮው በተለየና በከፋ መልኩ የቀጠለ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

        የምግብ እጥረት ማለት ምን ማለት ነው? እንደ ዩ.ኒ.ሴ.ፍ ትርጉም የምግብ እጥረት በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ተላላፊ (Recurrent Infectious Diseases) እና ሌሎች በሽታዎችን የሚያስከትል ችግር ነው፡ በአጠቃላይ የምግብ እጥረት ከመቀንጨር፣ መመንመን፣ ዥቅተኛ የሰውነት ክብደት፣ ያልተስተካከለ ወይም ልክ-ያልሆነ አካላዊ ዕድገት፣ የአዕምሮ ዕድገት ወስንነት፣ የማሰብና የመመራመር ችሎታ ማነስ፣ በሽታን የመከላከል ኃይል አልባ መሆንና ከህመም የማገገም አቅም ማነስ …. ወ.ዘ.ተ. ጋር በእጅጉ የተቆራኜ ችግር ነው፡፡

     የምግብ እጥረት ችግር ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ የሚገኙ አገራት ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ምንም እንኳን አገራችን ይህንን ችግር ለመቅረፍ ጥረት ብታደርግም የችግሩ አስከፊነት ደረጃ “አባይን በጭልፋ” ሆኖበታል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ከፍ ያለ ነዋየ-ፍሰት አድርጎ ተጨባጭ ስራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ የ“ኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብ ነክና ጤና ጥናት አገልግሎት” (Ethiopian Demographic and Health Service) በክልሎች ደረጃ ያለውን የምግብ እጥረት ስርጭት አስከፊነትን እነደሚከተለው አስፍሮታል፡፡ አፋር 49% ትግራይ 44% ደቡብ ህዝቦች 44% አማራ 42% ሲሆን እንደ ሃገር ደግሞ 40% እነደሆነ ዘገቧል፡፡ ይሁን እንጂ የስርጭት መጠኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲፈተሸ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሆኑን ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ ለምሳሌ ከ1990 እስከ 2014 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ውስጥ የችግሩ አስከፊነት ከነበረበት 39% ወደ 23% ዝቅ ብሏል፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 ዓ.ም የሕፃናት የመመንመን ችግር መጠን ከ100 ሕፃናት መካከል 7.5% ነበር፡፡ ይህም ማለት ከ13 ሕፃናት መካከል 1 ሕፃን ይመነምናል ነበር ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል የእኛን ጉዳይ ስንፈትሽ ደግሞ ሁኔታው የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ኢትዮጵያን በተመለከተ በ2001፣ 2006፣ 2008፣ 2009፣ 2011ና በ2012 ዓ.ም በተቋማት ደረጃ ችግሩን በተመለከተ ምንም ዓይነት ጥናት ያልተከናወነ በመሆኑ በቂ መረጃም ማግኜት አልተቻለም፡፡ በግል የተደረጉ ጥናቶች እነደሚጠቁሙት ግን በሃገራችን እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ ስር የሰደደ የምግብ እጥረት እነደነበር ጠቁመዋል፡፡ በሃገራችን ከ5 ዓመት ዕድሜ በታች በሚገኙ ሕፃናት ላይ የተከሰተውን የምግብ እጥረት እስከ 2015 ዓ.ም 30% እቀንሳለሁ ብሎ የተነሳው “4ኛው የኢዮጵያ ጤና ሴክተር እድገት ዕቅድ” (Fourth Ethiopian Health Sector Development Plan) 2011-2014/15 (HSDP) (37) ግቡን ሳይመታ ቀረ፡፡ የተመዘገበው ውጤትም ከዕቅዱ በታች በጣም አነስተኛ እንደነበር ተውቋል፡፡ ችግሩም ዓብይ አጀንዳ ሆኖ ወደፊት እንደሚቀጥልና በዚህ ችግር ሳቢያ የሚከሰተው ጤናማ ያልሆነ የሕፃናት አዕምመሯዊ፣ አስነልቦናዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊና አካላዊ እደገት ከፅንስ የሚጀምር ሲሆን ከድህረ-ልደት እስከ ሁለት ዓመት ዕድሜ በመቀጠል ጠባሳውን እንደሚያስቀምጥና የሕፃናትን በህይወት የመኖር ዕድል እንደሚወስን ተረጋግጧል፡፡ 

ሰላምና መልካሙን ሁሉ ለሕፃናትና ለሃገሬ ተመኘሁ!!

ሣህሉ ባዬ ዓለሙ

www.enrichmentcenters.org

የፕሮጄክት ማኔጅመንት፣ የሕፃናት ዕድገትና ስነልቦና ባለሙያ

 

 

 


  • SHARE IT ON

Comments

leave a comments

BECOME VOLUNTEER

“If our hopes of building a better and safer world are to become more than wishful thinking, we will need the engagement of volunteers more than ever.”